ፍትሃዊ የኢነርጂ ሽግግር

የታዳሽ ኃይል ቴክኖሎጂዎችን እና ዘላቂ የኃይል አማራጮችን ፍትሃዊ ተደራሽነት መደገፍ።

ለምን አስፈላጊ ሆነ

ፍትሃዊ የኢነርጂ ሽግግር አስፈላጊነት

ሃይል በተለይም ታዳሽ ሃይል ለዘላቂ ልማት እና ለኑሮ ደህንነት ወሳኝ ነው። ይሁን እንጂ በርካታ ጥናቶች እንደሚሳዩት ታዳሽ ኃይልን በተለይም በገጠር እና የተገለሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ ከማድረግ አንፃር ሰፊ ዉስንነቶች አሉ፡፡ ይህ ኢፍትሃዊነት የኢነርጂ ድህነትን ያስፋፋል፣ የህብረተሰብ ክፍሎችን ከብሄራዊ የኃይል ሽግግር ጥቅሞች እንዲገለሉ ያደርጋል፡፡ በመሆኑም ጥናትን መሰረት ያደረጉ ስራዎች መሰራት አለባቸዉ፡፡

ዓላማዎቻችን

  • በገጠርም ሆነ በከተማ በተመጣጣኝ ዋጋ፣ አስተማማኝ፣ ዘላቂ እና ዘመናዊ የሃይል አማራጮች ፍትሃዊ ተደራሽነትን ማስተዋወቅ እና ማሳደግ።
  • የፀሐይ፣ የውሃ፣ የንፋስ፣ የጂኦተርማል፣ ባዮ ኢነርጂ፣ አረንጓዴ ሃይድሮጅን እና ሌሎች አረንጓዴ ቴክኖሎጂዎችን ጨምሮ ታዳሽ የኃይል ምንጮችን ማልማት፣ ማላመድ እና አጠቃቀምን ማበረታታት።

በዚህ ፕሮግራም አብረውን ይሥሩ