የአረንጓዴ ፍትሕ ማጎልበት ማዕከል (አፍማማ) በኢትዮጵያ እና ከዚያም ባሻገር ያሉ ማህበረሰቦችን እየጎዱ ላሉ እያደጉ የመጡ የአካባቢ፣ የአስተዳደር፣ የኢነርጂ፣ የፍትሕ እና የሰብዓዊ መብት ተግዳሮቶች ምላሽ ለመስጠት የተቋቋመ ነው።
ማዕከሉ የአካባቢ ዘላቂነት፣ ማህበራዊ ፍትሕ፣ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር እና የማህበረሰብ ማብቃት እርስ በርሳቸው በጥልቅ የተሳሰሩ መሆናቸውን ይገነዘባል። እነዚህን ተግዳሮቶች ለመፍታት ማህበረሰቦችን በውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ማዕከል ላይ የሚያስቀምጡ የተቀናጁ መፍትሄዎች ያስፈልጋሉ።
ስለሆነም አፍማማ አረንጓዴ ፍትሕን እና ዘላቂ ልማትን ለማስፋፋት የሚያስችሉ የጥናት፣ የአድቮኬሲ፣ የሕግ ማብቃት፣ የአቅም ግንባታ፣ የፖሊሲ ተሳትፎ እና የአጋርነት ልማት መድረክ ሆኖ ይሠራል።
