አሳታፊ የአካባቢ አስተዳደር እና የማህበረሰብ ማብቃት

አሳታፊ አስተዳደርን፣ ያልተማከለ አሠራርን፣ ማህበራዊ ተጠያቂነትን እና የአካባቢ ተቋማትን ማጠናከር።

ለምን አስፈላጊ ሆነ

የባለብዙ ደረጃ አስተዳደር ዲሞክራሲያዊ ጉድለት

የህዝብ አስተዳዳር በተለይም በአከባቢ ደረጃ ያለው አስተዳደር ልማትን ወደ ፊት ለማራመድ እና ዴሞክራሲያዊ መረጋጋትን ለማስቀጠል ቁልፍ ሚና ይጫወታል። የአካባቢ አስተዳደር የአካባቢ መንግስታትን፣ ዜጎችን፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን፣ የግሉ ሴክተርን እና አንዳንዴም ሀገራዊ እና አለም አቀፋዊ አካላትን ጨምሮ ውስብስብ ተዋንያንን ያካትታል። ነገር ግን፣ በኢትዮጵያ፣ አሳታፊ አስተዳደርን ከማረጋገጥ አንፃር ሰፊ እና መዋቅራዊ ክፍተቶች እንዳሉ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ በዚህም ቁልፍ ባለድርሻ አካላት በተለይም የአካባቢ ማህበረሰቦች በኑሮአቸው እና በልማት ቅድሚያ የሚሰጧቸው ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ከሚያሳድሩ ውሳኔ ሰጪ ሂደቶች ላይ በተደጋጋሚ ይገለላሉ። በተጨማሪም፣ ማዕከላዊ የመሪነትና የማስተባበር ሚና የሚይዙት የአካባቢ መስተዳድሮች ራሳቸውን ችለው የተቋቋሙና በቂ አቅም ያላቸው አይደሉም። ይህ ባለድርሻ አካላትን ያገለለ አስተዳዳር እና የአካባቢ ምንግስታትን በሚፈለገዉ መልኩ አቅማቸዉን ማጎልበት አለመቻል የአስተዳደርን ጥራት፣ ህጋዊነት እና ዘላቂነት ያዳክማል፡፡ ይህም አስቸኳይ እና የታቀዱ የመፍትሄ እርምጃዎችን ይፈልጋል።

ዓላማዎቻችን

  • የትብብር፣ አሳታፊ እና ትስስር አሰራሮችን በማጠናከር ተጠያቂነት የተረጋጋጠበትና አሳታፊና መልካም የአካባቢ አስተዳደርን ማሳደግ።
  • የአካባቢ መንግስት ተቋማትን ጨምሮ የአስተዳደር ተዋናዮችን አቅም፣ ተጠያቂነት እና ምላሽ ሰጪነት ማሳደግ።
  • የአካባቢ መስተዳድሮችን ሚና ለማሳደግ እና የራስ ገዝ አስተዳደርን ለማጠናከር የሚያስፈልጉ የፖለቲካ፣ የአስተዳደር፣ የፊስካል እና የኢኮኖሚ አቅሞች ያልተማከለ ለማድረግ የሚስችሉ አሰራሮችን ማሳወቅና ማሳደግ።
  • ግልጽነትንና የዜጎችን ተሳትፎ ለማሳደግ የማህበረሰብ ተቋማትን ማብቃት እና የማህበራዊ ተጠያቂነት አሰራርን ማስተዋወቅ።
  • መብትን መሰረት ያደረጉ አካሄዶችን መደገፍ እና በፖሊሲ ቀረጻ እና ውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ላይ ትርጉም ያለው የህዝብ ተሳትፎ ማረጋገጥ።

በዚህ ፕሮግራም አብረውን ይሥሩ