ኃላፊነት የሚሰማው የመሬትና የተፈጥሮ ሀብት አስተዳደር

የይዞታ ዋስትናን፣ የመሬት አስተዳደር ሥርዓቶችን እና ማህበረሰብ-ተኮር የተፈጥሮ ሀብት አያያዝን ማጠናከር።

ለምን አስፈላጊ ሆነ

ኃላፊነት የሚሰማው የመሬት እና የተፈጥሮ ሀብት አስተዳደር ፍላጎት

በኢትዮጵያ መሬት እና ከመሬት ጋር የተያያዙ የተፈጥሮ ሀብቶች እጅግ ወሳኝ እና ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊ፣አካባቢያዊ እና ፖለቲካዊ ጠቀሜታ ያላቸው ናቸዉ፡፡ እንደ አለመታደል ሆኖ የመሬት መብቶችን ዕዉቅና በመስጠት፣በማስተዳደር እና በማስከበር ላይ ወሳኝ ክፍተት ይስተዋላሉ፡፡ ይህም የይዞታ ደህንነትን የሚጎዳ፣ መሬትን መሰረት ያደረጉ ግጭቶችን የሚያባብስ እና የህብረተሰቡን የተፈጥሮ ሃብት አያያዝ ወደ ጎን ገሸሽ የሚያደርግ ነዉ፡፡ እነዚህና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች አስቸኳይ ክትትልና ድጋፍ ይጠብቃሉ።

ዓላማዎቻችን

  • ፍትሃዊ፣ደህንነቱ የተጠበቀ እና ቀልጣፋ የመሬት እና የንብረት መብቶች ስርዓቶችን ማጎልበት እና ማስፈፀሚያ ስልቶችን ማጠናከር።
  • ፍትሃዊ ልማትንና የአካባቢ ደኅንነትን ለመደገፍ በከተማም ሆነ በገጠር ጤናማ የመሬት አስተዳደር እና ዘላቂ የመሬት አጠቃቀም አሰራሮችን ማሳደግ።
  • የአካባቢ ባለድርሻ አካላትን የሚያበረታቱ እና የስነ-ምህዳር ስርዓቶችን የሚጠብቁ ማህበረሰቡን መሰረት ያደረጉ፣ የተቀናጀ እና ቀጣይነት ያለው የተፈጥሮ ሃብት አያያዝ እና ጥበቃ ተግባራትን መደገፍ፡፡

በዚህ ፕሮግራም አብረውን ይሥሩ