በልማት ሂደት የሰብዓዊ መብት ጥበቃ

መብት-ተኮር ልማትን እና ተጋላጭ ማህበረሰቦችን ጥበቃ ማስፋፋት።

ለምን አስፈላጊ ሆነ

በልማት ሂደት የሰብዓዊ መብት ጥሰት

በትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶች ምክንያት የሚከሰቱ ያለፍላጎት መፈናቀሎች፣ የተገቢ ካሳ እጥረት እና በፋብሪካዎች መርዛማ ቆሻሻ ሳቢያ የሚፈጠረው የአካባቢ ብክለት የማህበረሰቡን በጤናማ አካባቢ የመኖርና ንጹሕ ውሃ የማግኘት ሰብዓዊ መብቶች የሚጥሱ በመሆናቸው፣ ማዕከሉ ማንኛውም የልማት ሥራ የአካባቢውን ተወላጆች መብት ባከበረ፣ ንቁ ተሳትፎን ባረጋገጠ እና ‘አረንጓዴ ፍትሕን’ በተከተለ መልኩ እንዲከናወን በሕግና በፖሊሲ ደረጃ ይሞግታል።

ዓላማዎቻችን

  • በትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶች ምክንያት የሚፈጠሩ ያለፍላጎት መፈናቀሎችን መከላከልና የአካባቢው ተወላጆች ተገቢውን ካሳ፣ ምትክ ቦታና የመልሶ ማቋቋም ድጋፍ እንዲያገኙ መሟገት።
  • በኢንዱስትሪዎች የሚለቀቁ መርዛማ ቆሻሻዎች የሚያስከትሉትን የአካባቢ ብክለት በመዋጋት የማህበረሰቡን ንጹሕ ውሃ የማግኘትና በጤናማ አካባቢ የመኖር ሰብዓዊ መብት እንዲከበር መስራት።
  • ማንኛውም ሀገራዊ የልማት እንቅስቃሴ የአካባቢውን ማህበረሰብ መብት ያከበረ፣ ንቁ ተሳትፎን ያረጋገጠ እና ‘አረንጓዴ ፍትሕን’ የተከተለ እንዲሆን የፖሊሲና የሕግ ጥናት ማካሄድና የጥበቃ (Advocacy) ሥራዎችን መሥራት።

በዚህ ፕሮግራም አብረውን ይሥሩ