አካባቢያዊ የሰላም ግንባታ እና ማህበራዊ ትስስር

የአካባቢ ትብብርን እና የሀብት አስተዳደርን በመጠቀም ሰላምን እና ማህበራዊ ትስስርን ማጎልበት።

ለምን አስፈላጊ ሆነ

አከባቢያዊ የሰላም ግንባታ እና ማህበራዊ ትስስር አስፈላጊነት

የአየር ንብረት ለውጥና የአካባቢ መራቆት እንደ ውሃ እና ለም መሬት ያሉ የተፈጥሮ ሃብቶችን በማሳሳት በማህበረሰቦች መካከል ለግጭት መንስኤ እየሆነ በመምጣቱ፣ ማዕከሉ እነዚህን የጋራ ሃብቶች በፍትሐዊነት ማስተዳደር እና አብሮ የመንከባከብ ባህልን በማሳደግ፣ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችን እንደ ማህበራዊ ትስስር እና መተማመን መፍጠሪያ መድረክ በመጠቀም ማህበረሰቡ ለጋራ ጥቅሙ በአንድነት እንዲቆምና ዘላቂ ሰላም እንዲገነባ ያደርጋል።

ዓላማዎቻችን

  • የአየር ንብረት ለውጥና የአካባቢ መራቆት የሚያስከትሉትን የተፈጥሮ ሃብቶች እጥረት ተከትሎ በማህበረሰቦች መካከል የሚነሱ ግጭቶችን መከላከል።
  • በተፈጥሮ ሃብቶች አጠቃቀምና አስተዳደር ላይ ፍትሐዊነት የሰፈነበት ሥርዓት እንዲገነባ በማድረግ ማህበረሰባዊ መተማመንን ማሳደግ።
  • የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችን እንደ ማህበራዊ ትስስር መፍጠሪያ መድረክ በመጠቀም ማህበረሰቡ ለጋራ ሃብቱ በአንድነት እንዲቆምና ዘላቂ ሰላም እንዲገነባ ማስቻል።

በዚህ ፕሮግራም አብረውን ይሥሩ