የአካባቢ ጥበቃ እና የአየር ንብረት ለውጥ

የአየር ንብረት ተቋቋሚነትን፣ ዘላቂ ልማትን፣ የብክለት ቁጥጥርን፣ የሥነ-ምህዳር መልሶ ማቋቋምን እና የአካባቢ አስተዳደርን ማስፋፋት።

ለምን አስፈላጊ ሆነ

የአካባቢ መራቆት እና የአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭነት

በኢትዮጵያ እንደአብዛኛዉ የአለማችን ክፍል የአካባቢ መራቆት እና የአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭነት ፈተናዎች ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመሩ ይገኛሉ። ይህም ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ስነ-ምህዳራዊ እና የህዝብ ጤና ቀውሶችን አስከትሏል። እነዚህ ተግዳሮቶች በዋነኛነት የሚከሰቱት ማህበረሰብን መሰረት ያደረጉ እና ስነ-ምህዳራዊ-ተኮር የአካባቢ ጥበቃ እና የአየር ንብረትን የመቋቋም ስልቶች ተነድፈዉ ባለመተግበራቸዉ ነዉ፡፡

ዓላማዎቻችን

  • ዘመናዊ የግብርና አሠራርን፣ አረንጓዴ ቴክኖሎጂዎችን፡ ኃላፊነት የሚሰማው የማዕድንና የኢንዱስትሪ ተግባራትን፣ የተቀናጀ እቅድን፡ አረንጓዴ የትራንስፖርት ስርዓትን፡ መቋቋም የሚችል መሰረተ-ልማትን፡ ለኑሮ ምቹ የሆኑ ከተሞችን፣ ቀልጣፋ የቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓትን እና ጠንካራ የመሬት፣ ወሳኝ ማዕድናት፣ ደን፣ የውሃ አካላት እና ሌሎች የተፈጥሮ ሃብቶች አስተዳደር እንዲሰፍን በማድረግ አካታችና ዘላቂ ልማትን መደገፍና ማስተዋወቅ።
  • የአየር፣ ውሃ፣ አፈር፣ ድምፅ፣ ብርሃን እና የሙቀት ብክለትን የተመለከቱ የብክለት ቁጥጥር ዘዴዎችን በማስተዋወቅ እና በልማት እቅድ እና ውሳኔ አሰጣጥ ውስጥ የማህበራዊ እና የአካባቢ ተፅእኖ ግምገማን በማበረታታት የአካባቢ ጥበቃን ማሳደግ።
  • የቅነሳና የመላመድ ስልቶችን እንዲሁም የአየር ንብረት ፋይናንስ የማዘጋጀትና የመዘርጋት ዘዴዎችን በማስተዋወቅ የአየር ንብረት ለውጥንና ተፅዕኖዎችን ለመከላከል የሚያስችሉ የተቀናጁ ጥረቶችን መደገፍ።

በዚህ ፕሮግራም አብረውን ይሥሩ