የፍትሕ ተደራሽነት

የሕግ ማብቃትን፣ የነፃ ሕግ ድጋፍን፣ የመብት ግንዛቤን እና ከፍትሕ ዘርፉ ጋር ትብብርን መስጠት።

ለምን አስፈላጊ ሆነ

የፍትህ ተደራሽነት እና የህግ ማብቃት ጉድለት

ፍትህ የፍትሃዊ የህግ ስርዓቶች እና የህዝብ አስተዳደር መለያ ምልክት ተደርጎ ይወሰዳል። ለዚህም ነው የፍትህ ተደራሽነት በብዙ አለም አቀፍ፣ ክልላዊ እና ሀገራዊ የሰብአዊ መብቶች ሰነዶች እውቅና ያገኘው። ነገር ግን በኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም የሴቶች፣ አርብቶ አደር እና የገጠር ማህበረሰቦች መብታቸውን ለመጠየቅ የሚያስችል ሃብትና እውቀት የላቸዉም፡፡ በተለይም መደበኛዉ የፍትህ ስርዓት ውስብስብ እና ተደራሽ ባለመሆኑ በሀገሪቱ ከፍተኛ የሆነ የፍትህ ክፍተት እየተፈጠረ ይገኛል፡፡ በዚህም አፋጣኝ እና ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ስራዎች መሰራት አለባቸዉ፡፡

ዓላማዎቻችን

  • ተገማች፣ ቀልጣፋ እና ጥራት ያለዉ ፍትህ ተደራሽነትን በመደበኛ ፍርድ ቤቶች፣ በማህበራዊ ፍርድ ቤቶች፣ በባህላዊ ተቋማት እና በዘመናዊ አማራጭ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች ማሳደግ።
  • ለተጋላጭ እና የተገለሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ነፃ የህግ ድጋፍ እና የበጎ ፍቃድ አገልግሎት መስጠት እና ማመቻቸት።
  • ግለሰቦች እና ቡድኖች መብቶቻቸውን እንዲረዱ እና እንዲጠቀሙ የሚያስችል ለንቃተ ህግ ግንዛቤ እና የአቅም ግንባታ ስራዎችን መደገፍ።
  • ግልጽነትን፣ ተጠያቂነትን እና ፍትሃዊነትን በመደገፍ በፖሊሲ እና ህግ ማውጣት እንዲሁም በአስተዳደር ኤጀንሲዎች የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች አስተዳደራዊ ፍትህን ማሳደግ።

በዚህ ፕሮግራም አብረውን ይሥሩ