ለምን አስፈላጊ ሆነ
ለታችኛው ፖሊሲ እና የህግ ማሻሻያ አስፈላጊነት
ዘርፈ-ብዙ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ የአካባቢ አስተዳደር ከማጠናከር ጎን ለጎን የፖሊሲ እና የህግ ማሻሻያዎችን ከታች ጀምሮ እስከ ላይ በሚደርሱ ሰንሰለቶች እንዲያልፉ ማድረግ ተቀባይነት እያኘ የመጣ አሰራር ነዉ፡፡ ነገር ግን፣ ኢትዮጵያ ውስጥ፣ ሁሉን አቀፍ ፖሊሲ ማውጣት ላይ ትልቅ ክፍተት አለ፡፡ የህዝብ ድምጽ በፖሊሲ እና ህግ ማዉጣት ሂደቶች ውስጥ እምብዛም አይካተትም። ይህ ክፍተት ብዙውን ጊዜ ከአካባቢው እውነታዎች ጋር የተንሰላሰሉ ፖሊሲዎችና ህጎች እንዳይወጡ ወይም ማሻሻያዎች እንዳይደረጉ ያደርጋል፡፡ ይህ ክፍተት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ንቁ ተሳትፎ እና ስልታዊ ድጋፍ ይጠይቃል።
ዓላማዎቻችን
- አካታች እና ምላሽ ሰጪ ፖሊሲ እና የህግ ማሻሻያዎችን ለማስጀመር የሚያስችሉ የአካባቢ ፍላጎቶችን እና አውድ እውነታዎችን መለየት እና በቅደም ተከተል ማስቀመጥ።
- ዜጎች እና ሌሎች የአካባቢ አስተዳዳር ግንባር ቀደም ተዋናዮች በፖሊሲ እና ህግ ማሻሻያዎች ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ማድረግና ማበረታታት።
- የአካባቢ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች የሚያንፀባርቁ፣ ፍትህን የሚያበረታቱ እና ዘላቂ ልማትን የሚያራምዱ የፖሊሲ እና የህግ ማሻሻያዎችን ማስጀመር እና መደገፍ።
በዚህ ፕሮግራም አብረውን ይሥሩ
